ጆን ረስኪን( John Ruskin) እንግሊዛዊ የስነ ጥበብ ሃያሲ ሲሆን ከ1819-1900 የኖረ በዘመኑ ከነበሩ ወደረኞቹ የቀደመ የሃሳብ ሰው ነበር። ረስኪን፣ “ረስኪንያዊ ዘይቤ” ተብሎ የተጠራለት የሀሳብ መንገድ በኪነ ህንፃ ላይ እንደጣለ ይታመናል። በ 1849 በታተመው 7ቱ የኪነ ህንፃ መርሆች (The Seven lamps of Architecture) በተሰኘው መፅሐፉ በኪነ ህንፃ ላይ ሊገቡ ግድ የሚሉ ናቸው ያላቸውን ሃሳቦች አቅርቧል። መስዕዋትነት፣...