በ2011፣ ነሓሴ ወር በስቱዲዮ ከተሰሩ ንድፎች መካከል አንዱ በሆነው በዚህ መልከዓ ምድራዊ ንድፍ (Landscape Design) ላይ ጐላ ብሎ የሚታይ የቅርጽ ስራ ይገኛል።ይህ ሥራ “The Thinker” ወይንም በግርድፉ ሲተረጐም አሳቢው የሚል ስያሜ ያለው ሲሆን በ1880 ዓ.ም በፈረንሳይ፣ ፓሪስ ከተማ ውስጥ August Rodin ፣ The Gates of Hell ወይንም የገሃነም መግቢያ በሮች ብሎ ከሰራው ጥቅል የጥበብ ሥራ...