ወደ አፍሪካ እንመለስ | Back To Africa

Embracing architecture is not for the few. It is not for the mere chosen. It is not only left for a certain elite. Rather it is a matter of decision. The decision you make when you comprehend a shelter & an architecture are quite distant.
POST-IT_2---Photo
POST-IT_1---Photo
POST-IT_3---Photo
POST-IT-4

በታላቁ የጥቁር መብት አቀንቃኝ በማርከስ ጋርቬይ የተጀመረና፣ከተፈጠሩበት ምድር ከአፍሪካ በባሪያ ስርዓት ለግዞት የተዳረጉ አፍሪካውያን ወደ ምድራቸው ለመመለስ በ18ኛው እና በ19ኛው ክፍለዘመን የተፈጠረው ንቅናቄ በብዙ ምክንያቶች ስኬታማ ሳይሆን ቢቀርም ዋናው ምክንያት የነበረው የባሪያ አሳዳሪ የነበሩት ነጮች የሃብትና የጉልበት ምክንያት የሆኗቸው ጥቁር ባሮቻቸው ከእጃቸው እንዳይወጡ እና የጥቁሮች መሰባሰብ ሀይል እንደሚሆን በማወቃቸው ነው።ትልቁ እውነታ ይህ ቢሆንም ብቸኛ ምክንያት አልነበረም።ከነጭ የባሪያ አሳዳሪዎች በተጨማሪ የግፍ አለቆቻቸው ምንዝር ለመሆን የፈቀዱ ጥቁሮችም ይህ እንቅስቃሴ እንዳይሳካ ብዙ አድርገዋል።
ይህን ታሪካዊ ትግል ማሳያ በማድረግ በተሰራው በዚህ መሠረታዊ ንድፍ(Basic Design) ከታላቁ መሪ ማርከስ ጋርቬይ ጀምሮ የተነሱትን ጥቁሮች በዳይናሚክስ የንድፍ መርህ ወደ አንድ አቅጣጫ የሚጓዙ ጥቋቁር ቋሚዎች (Vertical Elements) ተወክለዋል።ይሁንና ከመጀመሪያው ወይንም ከመሪው በኃላ ያሉት ተጓዦች በአካላቸው ላይ እየተባዙ የሚሰፍሩት ነጫጭ ነጠብጣቦች በጥቁር አፍሪካውያን ላይ በጊዜ ሂደት እና በፈቃድ የተቀየረውን የማንነት እውነታ ያሳያል።በጉዞውም ላይ የሚጓዙት በሻከረ ነጭ መደብ መሆኑ አፍሪካውያን በወቅቱ የነበሩበትን ጨካኝ (Cruel) ዓለም ሲያመለክት በሌላኛው ፅንፍ ደግሞ ማንነታቸውን የሚያንፀባርቅ በንፁሕ አድማሳዊ እይታ ያደበበ ምድር ይታያል።
የአፍሪካውያኑ ጉዞ ከላይ በታሪኩ እንደታየው ስኬታማ ባለመሆኑ ሁሉም ቋሚዎች የተስፋቸውን ምድር ሲረግጡ አይታይም።የዚህ ምክንያት የሆኑትን ለመግለጽ ደግሞ አብዛኞቹ ቋሚዎች በነጭ ገመዶች ወደኋላ ሲጎተቱ ይታያሉ።ነገርግን የመጨረሻዎቹ ሁለቱ በጥቁር ገመዶች የሚጎተቱ ሲሆን ይህም አፍሪካውያን በራሳቸውም ወገኞች እንደሚወድቁ ማሳያ ነዉ።
ኪነ ህንፃዊ ንድፍ እንደዚህ ባሉ ጉልበታም ፅንሰ ሃሳቦች መሠረትነት ሲነደፍ ከቁስነት ባለፈ ከስሜት፣ከጥልቅ እሳቤ እና ከተፈጥሮ ትርጓሜ የተዋቀረ ጥበብን መፍጠር ይቻለዋል።
[ በ2004ዓም ሰኔ ወር በተማሪነት ለመጀመሪያ ዓመት የመሠረታዊ ንድፍ(Basic design course 2)መዚጊያ የተሰራ ሀሳባዊ(conceptual)የንድፍ ስራ ]
@Gediyon’s Design Studio
#ኪነ ህንፃን እናወድስ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

https://gediyonsdesignstudio.com/wp-content/uploads/2020/12/Untitled-2png.png

Let’s design together

Embracing architecture is not for the few. It is not for the mere chosen. It is not only left for a certain elite. Rather it is a matter of decision.The decision you make when you comprehend a shelter & an architecture are quite distant.
Social
[bt_bb_instagram number=”10″ hashtag=”adhoc” client_id=”8f34d96ce4614e9fb349028703ea2aaa” access_token=”3294319514.8f34d96.b089a3d99be8493eb1e0e0949ab6bc84″ el_id=”” el_class=”” el_style=”” columns=”5″ gap=”no_gap”][/bt_bb_instagram]

Copyright by Gediyon’s Design Studio . All rights reserved.