ጆን ረስኪን( John Ruskin) እንግሊዛዊ የስነ ጥበብ ሃያሲ ሲሆን ከ1819-1900 የኖረ በዘመኑ ከነበሩ ወደረኞቹ የቀደመ የሃሳብ ሰው ነበር። ረስኪን፣ “ረስኪንያዊ ዘይቤ” ተብሎ የተጠራለት የሀሳብ መንገድ በኪነ ህንፃ ላይ እንደጣለ ይታመናል። በ 1849 በታተመው 7ቱ የኪነ ህንፃ መርሆች (The Seven lamps of Architecture) በተሰኘው መፅሐፉ በኪነ ህንፃ ላይ ሊገቡ ግድ የሚሉ ናቸው ያላቸውን ሃሳቦች አቅርቧል። መስዕዋትነት፣ ሀቅ፣ ሀይል፣ ስነ ውበት፣ ህላዌ፣ ትውስታ እና መታዘዝን የህንፃዎች ተፈጥሮአዊ ማንነት መሆን እንደሚገባቸው የኪነ ህንፃ ባለሞያዎችን ሞግቷል። ተመልካቹንም፣ ህንፃዎች በሚፈጥሩት የጥበብ ልክ እና የፈጠራ ዓለም እንዲገነዘቧቸው በመፅሓፉ እንዲህ ያሳስባል••••
“Don’t just look at buildings… Watch them!”
“ህንፃዎችን ከማየት ባለፈ… ተመልከቷቸው!”